የአፍሪካ ጄንደር ኢኖቬሽን ላብ የኢትዮጲያ የፆታ እኩልነት ጥናት አፍሪካ ጄንደር ኢኖቬሽን ላብ አፍሪካ ጀንደር ኢኖቬሽን ላብ ከሰሀራ በፆታ እኩልነት ዙርያ ለመሥራት አስፈላጊ የመረጃ ስንቅ በታች ባሉ አገሮች ላይ አተኩሮ የተለያዩ የልማት ነክ ድጋፎችን እና እያመጡ ያሉትን ውጤት በጥልቀት ለመመርመር የተቋቋመ አካል ነው፡፡ ተቋሙ በተለይ መግቢያ ትኩረት ሰጥቶ የሚሠራው ከሰሀራ በታች ባሉ አገሮች የፆታ እኩልነትን ለማስፈን ባለፉት አስር ዓመታት ኢትዮጵያ አስደናቂ የኢኮኖሚ ዕድገት እያስመዘገበች ትገኛለች፡፡ ይህም እና በገቢ፣ በምርታማነት፣ በንብረት ይዞታ እና በውክልና ዙርያ ያለውን የፆታዎች በፈጣን የምጣኔ ሀብት ዕድገት (የአገር ውስጥ ምርት ወይም ጂ.ዲ.ፒ ዕድገት) እና ፈጣን አለመጣጠን ለመቀነስ ነው፡፡ የድህነት ቅነሳ ይገለፃል፡፡ ነገር ግን ከእነዚህ ስኬቶች በስተጀርባ አሁንም ፈታኝ ሥራዎች የፆታ ልዩነትን ለማጥበብ መሰረታዊው ነገር የችግሩን ጥልቀት በተመለከተ በቂ የሚቀሩ መሆኑን ማየት ይቻላል፡፡ ከነዚህም መካከል በፆታ እኩልነት ዙርያ ያለው ክፍተት ሲሆን፣ መረጃ መያዝ እንደመሆኑ መጠን ተቋሙ በጉዳዩ ዙርያ በቂ እውቀት ለመገንባት ይህም ሁሉን አቀፍ ዕድገት ከማምጣት አንፃር፣ እንዲሁም የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም አሟጦ እየሠራ ነው፡፡ የአፍሪካ ጄንደር ኢኖቬሽን በመጠቀም ረገድ ብዙ መሠራት እንዳለበት አመላካች ነው፡፡ በኢትዮጵያ አሁንም ሴቶች ከወንድ ላብ የጥናት ቡድን በአሁኑ ወቅት በ21 አገሮች 60 የተለያዩ የጥናት መስኮች ላይ አቻዎቻቸው በበርካታ የኢኮኖሚ መመዘኛዎች እና አመላካቾች ወደኋላ ቀርተው የሚታዩ እየሠራ የሚገኝ ሲሆን፣ ዋናው ዓላማውም ሲሆን፤ በተለይ በሥራ ዘርፍ በግብርና ምርታማነት፣ ከሥራ ፈጠራ በሚገኝ ገቢ፣ እንዲሁም በጥናት ላይ ተመሥርቶ የችግሮችን ልክ መተንተን እና ለቀጠናው አገሮች በደሞዝ ገቢ ደረጃ ይህ ልዩነት በግልጽ ይታያል፡፡ ሴቶች በትምህርት፣ በጤና፣ መሠረታዊ የሆኑ ጠቃሚ ልምዶችን መቀመር ነው፡፡ ሰብዓዊ መብቶችን በመጐናፀፍ ደረጃ ከወንድ አቻዎቻቸው እኩል ተጠቃሚ መሆን አልቻሉም፡፡ የልማት ነክ ድጋፎችን ውጤት እነዚህ ክፍተቶች በአብዛኛው በአገሪቱ ማኅበራዊ እሴቶች ላይ ተመስርተው እያደጉ የመጡ በጥልቀት መመርመሩ ለመንግሥታት፣ የልማት ተቋማት እና የግሉ ዘርፍ በመሆኑ በአጠቃላይ የድህነት ቅነሳ እና የኢኮኖሚ ዕድገቱ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ማሳደራቸው ውጤታማነታቸው ተፈትኖ የተረጋገጠ አይቀሬ ነው፡፡ የፖሊሲ አማራጮችን ለማቅረብ የሚያስችል ሲሆን፣ ይህም በአፍሪካ ደረጃ የፆታ እኩልነትን ለማረጋገጥ ቁልፍ ምንም እንኳን መንግሥት የፆታ እኩልነት ክፍተቶችን ለማጥበብ በከፍተኛ ቁርጠኝነት መሥሪያ እንደሚሆን ያምናል፡፡ በጥናት የመዋዕለ ንዋይ ፈሰስ በማድረግ እየሠራ ቢሆንም ከአዳዲስ ጥናቶች የሚገኘው ወሳኝ ላይ የተመሠረተ ዕርምጃ የአህጉሪቱ ፈተና የሆነውን የፆታ ልዩነት ከመሠረቱ መረጃ የመንግሥት የሀብት ፍሰት የተሻለ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ እንዲይዝ ያስችላል ብለን ለማስወገድ እና የሴቶችን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እናምናለን፡፡ በመሆኑም በአፍሪካ ጄንደር ኢኖቬሽን ላብ (ጂ.አይ.ኤል) የተጠናቀረው ጥናት አይነተኛ መሳሪያ መሆኑንም ያምናል፡፡ ዘመናዊ የጥናትና ትንተና መንገዶችን በመጠቀም የኢትዮጵያ የፆታ እኩልነት ክፍተቶች በመሆኑም አፍሪካ ጄንደር ኢኖቬሽን ላብ በፆታ እኩልነት ዙርያ ያለውን መሠረታዊ መንስኤ፣ እንዲሁም ዋና ዋና ግፊት የሚያሳድሩ ምክንያቶችን ለይቶ ለማስቀመጥ የእውቀት እና የመረጃ ክፍተት መሙላት፣ ሙከራ አድርጓል፡፡ በዚህ መሠረት ጥናቱ የመጨረሻውን ዙር የኢትዮጵያ ሶሺዎ-ኢኮኖሚክ እንዲሁም ለፖሊሲ አውጪው ግብዓት የሚሆኑ ትርከቶችን እና መረጃዎችን ሰርቬይን (Socioeconomic Survey) (2015-2016) እንደ ዋነኛ የመረጃ ምንጭ በመጠቀም፣ አዘጋጅቶ ማቅረብ፣ ብሎም የፆታ እኩልነት ጉዳይ ዙርያ በቂ ግንዛቤ በመፍጠር ውጤታማ ሊሆኑ የሚችሉ ይህ የፖሊሲ ማስታወሻ የኣለም ባንክ አፍሪካ ጀንደር ኢኖቨሽን ላብ ባዘጋጀዉ የኢትዮጵያ የፆታ እኩልነት ጥናት ሪፖርት ላይ የተመሰረተ እና የማይችሉ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ነው። ጥናቱን ያዘጋጁት ኒክላስ ቢዩህረን ፣ ማርከስ ጎልድስቲን ፓውላ ጎንዛሌዝ ፣ አድያም ሃጎስ ፣ ዳንኤል ከርክዉድ ፣ ፓትሪሽያ ፓስኮቭ ማመላከት ችግሩን ለመፍታት ፣ ሚሼል ፖሊን እና ቻንድኒ ራጃ ናቸው። መሠረታዊ ነው ብሎም ያምናል፡፡ http://www.worldbank.org/en/programs/africa-gender-innovation-lab እንዲሁም የተመሰከረላቸውን ስታቲስቲካዊ የጥናት ዘዴዎችን1 በመገልገል በሥራ ቅጥር፣ በግብርና ምርታማነት፣ እንዲሁም በሥራ ፈጠራ እና መደበኛ የቅጥር ገቢ ዙርያ በፆታዎች መካከል የሚስተዋለውን ከፍተኛ ልዩነት ለመተንተን ሙከራ አድርጓል፡፡ ከዚህ በመነሳት ጥናቱ መንግሥት ሊያተኩርባቸው የሚገቡ የፖሊሲ ዘውጐችን ያስቀመጠ ሲሆን፣ እነዚህ ምክረ-ሐሳቦች ሴት ሠራተኞች፣ አርሶ-አደሮች እና የንግድ ድርጅት ባለቤቶች የሚያጋጥሟቸውን ማነቆዎች ከማስወገድ አንፃር ወሳኝ የሚባሉ ነጥቦች ናቸው፡፡ በመቀጠልም የጥናቱ ግኝቶች እና የፖሊሲ ምክረ-ሐሳቦች በጥልቀት የሚዳስሱ ይሆናል፡፡ ቁልፍ ግኝቶች 1.  በጥቅሉ ሴቶች ከወንድ አቻዎቻቸው ያነሰ ሥራ የማግኘት/የመቀጠር ዕድል ያላቸው ሲሆን፣ ሥራ የማግኘት ዕድል ቢኖራቸው እንኳ ከወንዶቹ ያነሰ ሰዓት (በሳምንት) ለመሥራት እንደሚገደዱ ጥናቱ ያመለክታል፡፡ በተጨማሪም ሴቶች ከወንድ አቻዎቻቸው ያነሰ በመደበኛ ሥራ ተቀጥሮ የመሥራት ዕድል ያላቸው ሲሆን፣ በአብዛኛው ከግብርና ጋር ባልተያያዙ የሥራ ዘርፎች ተቀጥሮ የመሥራት ዕድላቸው ሰፊ ሆኖ ይታያል፡፡ በአጠቃላይ ኢትዮጵያዊ ሴቶች ከወንድ አቻዎቻቸው በ17 በመቶ ያነሰ ሥራ የማግኘት ዕድል ያላቸው ብቻ ሳይሆን ሥራ ቢያገኙም እንኳን በአማካይ በሳምንት ከወንዶች 4.4 ሰዓታት ያነሰ ጊዜን በሥራ ላይ ያሳልፋሉ፡፡ (ስዕላዊ መግለጫ 1ን ይመልከቱ)2 ከዚህ ባለፈ የሴቶች ሥራ የመሥራት ወይም ያለመሥራት እንዲሁም ስንት ሰዓት የመሥራት ዓይነት ውሳኔዎቻቸው በአብዛኛው በግል እና በቤተሰባዊ ባህሪያት ላይ የሚመሠረቱ ሲሆን፣ ከብዙ በጥቂቱ ዕድሜ፣ የቤተሰብ መሪ መሆን-ያለመሆን፣ የትዳር ሁኔታ፣ የትምህርት ደረጃ፣ የጤነነት ሁኔታ፣ የብድር አቅርቦት ተደራሽነት ጉዳይ፣ የተከማቸ ሀብት ሁኔታ፣ የቤተሰብ ቁጥር ብዛት፣ የጥገኛ/የልጆች ምጣኔ፣ እንዲሁም የመኖሪያ ስፍራ የመሳሰሉ ጉዳዮች ይገኙበታል፡፡ ለምሳሌ ያህል ከላይ በተዘረዘሩ ባህርያት መስፈርትነት ተመሳሳይ የሕይወት ደረጃ ላይ የሚገኙ ወንዶችን እና ሴቶችን ስንመለከት በተለይ ሥራ በማግኘት ረገድ ከፍተኛ ልዩነቶች ተንፀባርቀዋል፡፡ ይህም ሲባል ሴቶች ከወንድ አቻዎቻቸው በ29 በመቶ ያነሰ ሥራ የማግኘት ዕድል አላቸው፡፡ ለመገመት እንደሚቻለው በሥራ ላይ የሚጠፋ ጊዜ በቀጥታ ከኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ጋር የሚያያዝ ነገር ነው፡፡ በዚህ ረገድ በጊዜ እጥረት ምክንያት የሚመጣ ድህነት ለሴቶች በእጅጉ ፈታኙ ማነቆ ሲሆን፣ ይህም በዋናነት ሴቶች ከወንዶች ይበልጥ በቤተሰብ ዙርያ ላሉባቸው ኃላፊነቶች ትኩረትና ጊዜ የሚሰጡ ከመሆኑ የመነጨ እንደሆነ አያጠራጥርም፡፡ በሌላ በኩል ሴቶች ከወንዶች በተሻለ ከግብርና ጋር ባልተገናኙ ዘርፎች/ንግዶች የመሥራት ዕድላቸው ከፍ ያለ እንደሆነ ጥናቱ ያሳያል፡፡ ይህም በዚህ ዘርፍ ከሚሠሩ ሠራተኞች ግማሾቹ ሴቶች እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ በሌላ በኩል ሴቶች በመደበኛ ሥራም ሆነ የግብርና ዘርፉ የመሥራት ዕድላቸው ከወንድ አቻዎቻቸው ያነሰ ሲሆን፣ ይህም በነዚህ ሁለት ዘርፎች በሚታየው ከ40 በመቶ በታች የሴቶች ተሳትፎ የሚገለጽ ነው፡፡ ሴቶች በመደበኛ ወይም መደበኛ ባልሆነ ዘርፍ ተቀጥረው የመሥራት ዕድላቸውን በመወሰን ደረጃ ክህሎት የሚጫወተው ሚና በእጅጉ ትልቅ ነው፡፡ በዚህ መሠረት ዝቅተኛ ክህሎት ያላቸው ሴት ሥራ ፈላጊዎች ከመደበኛው ይልቅ መደበኛ ባልሆነው ዘርፍ የመቀጠር ዕድላቸው ሰፊ ነው፡፡ በመሆኑም ውስን የሥራ ክህሎት ያላቸው ሴቶች የሥራ-አጥ ቋቱን ለመቀላቀል ሰፊ ዕድል አላቸው፡፡ በተለይ በከተማ አካባቢ ይህ እውነታ በስፋት የሚስተዋል ነገር ነው፣ ከዚህ ባለፈ ሴቶች በአብዛኛው ጊዜያዊ የሥራ ዘርፎች ላይ ተሰማርተው ይታያሉ፡፡ ከጊዜያዊ ሥራ የሚገኘው ገቢ ዝቅተኛ መሆኑ በራሱ አመላካች ቢሆንም ከዚያ የባሰው ግን ጊዜያዊ ሠራተኞች እንደ የሥራ ላይ ሥልጠና ዓይነት ክህሎትን የሚጨምሩና አቅምን ለማጎልበት የሚያሰችሉ አጋጣሚዎችን የሚፈጥሩ ዕድሎችን መጠቀም እንዳይችሉ በማድረግ ለዘላቂው የሴቶችን የተሻለ ሥራ የማግኘት ዕድል ማጨለሙ ነው፡፡ በሥራ ገበያው ላይ ተፈላጊ የሆነ ክህሎትን በተመለከተ በፆታዎች መካከል ያለውን ልዩነት ማጥበብ በሴቶች የኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ላይ ካለው ከፍተኛ ተፅዕኖ ባለፈ በአጠቃላይ የማኅበረሰቡ ኢኮኖሚያዊ አቋም ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ ያመጣል፡፡ የሴቶች በሥራ ገበያው ላይ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እና የትምህርት ደረጃ መሻሻል በቀጥታ ከኢኮኖሚ ዕድገቱ ፍጥነት ጋር የሚገናኝ ጉዳይ ሲሆን፣ ከዚያ ባለፈም የሕፃናት ሞትን በመቀነስ፣ እንዲሁም በእናቶች እና ሕፃናት ጤንነት ዙርያ የሚታይ እመርታን ለማስመዝገብ ያስችላል፡፡ የተሻለ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ደግሞ የሴቶችን የውሳኔ ሰጪነት ሚና በእጅጉ የሚያሻሽል ብቻ ሳይሆን በጥቅሉ በልጆች ጤና፣ አመጋገብና እና ትምህርት ዙርያ ቤተሰቡ የሚያወጣውን ወጪ እንዲጨምር ጥሩ መነሻ ይሆናል፡፡ በጥቅሉ እነዚህ ሁሉ በግለሰብ ደረጃ የሚመዘገቡ መሻሻሎች ዞሮ ዞሮ በኢኮኖሚ ዕድገቱ እና ምርታማነት በመጨመሩ ረገድ ያላቸው ሚና ትንሽ የሚባል አይደለም፡፡ ኦክሳካ-ብላይደር ዲኮምፖዚሽን ዘዴ በመባል የሚታወቀው ስታቲስቲካዊ መሣሪያ በሁለት የመረጃ መደቦች መካከል በተለይ በሁለቱ ዲፔንደንት ቫሪያብል የሚን ምጣኔ መካከል ያለውን ልዩነት 1  የሚያብራራ ሲሆን፣ ይህም ልዩነቱን (ጋፕ) ሁለት ቦታ በመክፈል ማለትም የኢንዶውመንት ተፅዕኖ እና የስትራክቸራል ተፅዕኖ ብሎ በመለየት የሚከናወን ነው፡፡ የኢንዳውመንት ተፅዕኖ የሚያሳየው በፆታዎች መካከል ያለውን ልዩነት በተለይ ከመሠረታዊ የምርት ግብዓቶች አጠቃቀም አንፃር ያለውን ልዩነት ሲሆን፣ ይህም የሥራ ልምድን፣ አጠቃላይ የምርት ግብዓትን ወይም የብድር አቅርቦትን የመሳሰሉ መመዘኛዎችን ታሳቢ በማድረግ ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ በፆታዎች መካከል የተፈጥሮም ሆነ ሰው ሰራሽ ሀብት አጠቃቀም አንፃር ያለውን ልዩነት ያሳያል፡፡ ስትራክቸራል ተፅሀኖ ደግሞ ከላይ የተጠቀሱትን ሀብት እና የምርት ግብዓትን በመጠቀም የሚገኙ ውጤቶችንና የምርታማነት ልዩነቶችን ይገመግማል፡፡ በዚህ ረገድ በፆታዎች መካከል ማወዳደር ሲደረግ በተቻለ መጠን ተመሳሳይ የሥራ ልምድ ወይም ተመሳሳይ የግብዓት አጠቃቀም ባላቸወ ዙርያ ብቻ ይሆናል፡፡ በሌላ አገላለጽ ስትራክቸራል ተፅዕኖ የፆታ መድሎ እና ሌሎች ልዩነት ፈጣሪ ምክንያቶች (ከሥራ ልምድ እና የግብዓት አጠቃቀም ውጪ) አንጥሮ የሚያሳይ ነው 2 እነዚህ ግኝቶች መሠረት ያደረጉት በአገር አቀፍ ደረጃ ወካይ ሊባል የሚችል 13,316 በሥራ የመሥሪያ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ግለሰቦች ናሙና ላይ ሲሆን ናሙናው ከ14 ዓመት በላይ የሆኑ ግለሰቦችን ሲወስድ፣ ከእነዚህም ውስጥ 52 በመቶ ሴቶች ናቸው፡፡ 2 2.  በዋነኝነት በምርት ግብዓቶች ልዩነት ምክንያት የሴቶች የግብርና ምርታነት ደረጃ ከወንድ አቻዎቻቸው አንሶ ይታያል፡፡ በኢትዮጵያ ሴት የማሳ አስተዳዳሪዎች ከወንድ አስተዳዳሪዎች በሔክታር 36 በመቶ ያነሰ ምርት ያመርታሉ፡፡3 ነገር ግን ተጨማሪ ግለሰባዊ፣ ቤተሰባዊ እንዲሁም የማምረቻ መሬቱን ባህርያት ከግምት ውስጥ ሲገቡ የምርታማነት ልዩነቱ ወደ በሔክታር 6 በመቶ ዝቅ ይላል፡፡ ይህም በዋነኝነት የሚያሳየው ተጨማሪ ባህርያቱ ለግብርና ምርታማነት ልዩነቱ ያላቸውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነው፡፡ እንዲያውም በጥናቱ መሠረት የተጠቀሱት ባህርያት ለምርታማነት ልዩነቱ መፈጠር የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡ ምንም እንኳን ግለሰባዊ እና ቤተሰባዊ ባህርያቱ ከደምግራፊክ ምክንያቶች ጋር ተደምሮው በግብርና ምርታማነት ዙርያ የሚታየውን የፆታ ልዩነት የሚገልፁት ቢሆንም አሁንም ቢሆን በአብዛኛው የዚህ የምርታማነት ልዩነት ጉዳይ በአጠቃላይ በምርት ግብዓቶች መጠን ምክንያት የሚፈጠር ልዩነት መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በዚህ ረገድ ሴቶች በአጠቃላይ የግብርና ኤክስቴንሽን ግልጋሎትን በማግኘት ረገድ፣ ለመደበኛ የብድር አቅርቦት ተደራሽ ከመሆን አንፃር፣ ዘመናዊ ግብዓቶችን ከመጠቀም እና በዓይነታቸው የተሰባጠሩ ምርቶችን ከመዝራት አንፃር ከወንድ አቻዎቻቸው አንፃር ክፍተቶች ይታያሉ፡፡ በመሆኑም በግብርና ምርታማነት ረገድ የፆታ ልዩነቱን ለማጥበብ ሴቶች በአጠቃላይ ለምርት ግብዓቶች ያላቸውን ተደራሽነት ማሻሻል አማራጭ የሌለው ዕርምጃ ነው፡፡ በዚህ የፆታ ልዩነት እና ምርታማነት ልዩነት ዙርያ ያሉ ተጨማሪ ነጥቦች ከታች ቀርበዋል፡፡ ስዕላዊ መግለጫ 1፡ የፆታ ልዩነት በሥራ ገበያው፣ በግብርና ምርታማነት፤ እንዲሁም በግል እና በቅጥር ሥራ ገቢ ደረጃ በሴት እና በወንድ መካከል ያለ ልዩነት ባለፈው ሳምንት በትንሹ አንድ ሰዓት የሠራ/ች 17%*** የግብርና ምርታማነት 36%*** በግል ከሚደረግ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የተገኘ ገቢ 79%*** ከቅጥር (ሥራ) የተገኘ ገቢ 44%*** 0% 10% 20% 30% 40% 50% 60% 70% 80% 90% 100% በግልፅ የሚታዩ ባህርያት ከግምት ገብተው የታየ ልዩነት ባለፈው ሳምንት በትንሹ አንድ ሰዓት የሠራ/ች 29%*** የግብርና ምርታማነት 6% በግል ከሚደረግ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የተገኘ ገቢ 24%** ከቅጥር (ሥራ) የተገኘ ገቢ 36%*** 0% 10% 20% 30% 40% 50% 60% 70% 80% 90% 100% ማስታወሻ፡ */**/*** እነዚህ ምልክቶች በ10 በመቶ፣ 5 በመቶ እና 1 በመቶ ደረጃ ያለውን ስታቲስቲካዊ ትርጉም (Significance) የሚያመለክቱ መሆኑን ልብ ይሉዋል፡፡ እነዚህ ግኝቶች መሠረት ያደረጉት በአገር አቀፍ ደረጃ ወካይ ሊባል በሚችል የ 2907 አርሶ-አደሮች ናሙና ላይ ሲሆን ፣ ከእነዚህም ውስጥ 21 በመቶው ሴቶች ናቸው፡፡ 3  3 ሴት አርሶ-አደሮች የግብርና ኤክስቴንሽን ፕሮግራሞች ላይ ተሳታፊ በመሆን ረገድ ከወንድ አቻዎቻቸው በ11 በመቶ ያነሰ ዕድል አላቸው፡፡ በመሆኑም ይህ ልዩነት በግብርና ምርታማነት ዙርያ በፆታዎች መካከል የሚስተዋለውን ልዩነት ይበልጥ ያሰፋዋል፡፡ ሴቶች ለግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎት ተደራሽ የመሆንና ያለመሆን ዕድል በአቅርቦት እና ፍላጐት ረገድ የሚስተዋሉ ማነቆዎች ላይ ይመሠረታል፡፡ በአቅርቦት በኩል ስንመለከት ከላይ ወደታች የሚወርደው የግብርና ኤክስቴንሽን ሞዴል (ፍልስፍና) በአብዛኛው ወንዶችን ከሴት ገበሬዎች በተሻለ ቅድሚያ ሲሰጥ ይስተዋላል፡፡ ይህ የሆነው ግልጋሎቱ በአብዛኛው ‹‹ሞዴል›› ወይም የግብርና ‹‹ተራማጅ›› ተብለው የሚመረጡ አርሶ አደሮች ላይ አተኩሮ የሚሠራ በመሆኑ ሲሆን፤ ይህ እሳቤ በዋነኝነት እነዚህ የተመረጡ ኤክስቴንሽን አርሶ-አደሮች የግብርና ቴክኖሎጂዎችን እና ግብዓቶችን በተሻለ ይተገብሩታል ብሎም ለሌሎች አርሶ አደሮች ያስተላልፉታል አገልግሎት በሚል ነው፡፡ በፍላጐት ወገን ያየነው እንደሆነ በገጠር የሚኖሩ ሴቶች በተለይ በትምህርት እና መረጃ ተደራሽነት ውስን መሆን ተደራሽነት ብሎም በቂ ተመጋጋቢ የምርት ግብዓቶችን ባለማግኘታቸው ምክንያት፣ በተለይ በቴክኖሎጂ እና አገልግሎት ዙርያ የሚጠቅማቸውን ለይተው የመጠየቅና የማግኘት ዕድላቸው ላይ ተፅዕኖ ሲያሳድር ይስተዋላል፡፡ በአጠቃላይ በእማወራዎች የሚተዳደሩ የግብርና ቤተሰቦች ከወንድ አቻዎቻቸው በአማካይ የ 9 መቶኛ ነጥቦች (Percentage points) ያነሰ ብድር የማግኘት ዕድል አላቸው፤ ይህም የፆታ ልዩነትን የሚያሰፋ ሌላኛው ምክንያት ነው፡፡ በሌላ በኩል ሴቶች የብድር አቅርቦት ተደራሽነታቸውን በእጅጉ የሚቀንሰው ጉዳይ ሴቶች የራሳቸው የሆነ ንብረትን የመያዝ ዕድላቸውን ጠባብ የሚያደርጉ አሠራሮች ሲሆኑ፣ ይህም ብድር ለማግኘት የሚያስፈልገውን ማስያዣ የማቅረብ ብቃታቸውን ብሎም ብድር የማግኘት ዕድላቸውን የተመናመነ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም ሴቶች በማኅበረሰቡ ዘንድ ያላቸው ዝቅተኛ የማኅበራዊ የብድር አቅርቦት ካፒታል (Social and human capital) ብድር ለማግኘት ብቁ እንዳይሆኑ እያደረገ ይገኛል፡፡ ተደራሽነት በኢትየጵያ በአማካይ ሴት የማሳ አስተዳዳሪዎች 0.6 ሔክታር መሬት እንደሚያርሱ መረጃዎች የሚያሳዩ ሲሆን፣ ይህም ከወንድ አቻዎቻቸው 1 ሔክታር ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ልዩነት አለው፡፡ ከዚህ ባለፈም ሴቶች ለምርት የሚመርጧቸው የሰብል ዓይነቶች ውስን መሆን እና ይህም ከወንድ አቻዎቻቸው አንፃር ከፍተኛ ልዩነትን የሚያሳይ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ እንደሚታወቀው የማሳ ስፋት እና የግብርና ምርታማነት በእጅጉ የተሳሰሩ ጉዳዮች ናቸው፡፡ በዚህ መሠረት ሴት አርሶ-አደሮች በአማካይ አነስተኛ ማሳ የሚያርሱ መሆኑ እና የማሳ ስፋት ባነሰ ቁጥር ደግሞ ምርታማነት የመጨመር አዝማሚያ የሚያሳይ በመሆኑ አነስተኛ የማሳ ስፋቱ የማሳ ስፋት የፆታ ልዩነቱ እንዳይሰፋ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ ነገር ግን ውስን የሰብል ዓይነቶች ላይ የተመሠረተው ግብርና ግን በግብርና እና የሰብል ምርታማነት ዙርያ የሚስተዋለውን የፆታ ልዩነት እንደሚያሰፋው መረዳት ይቻላል፡፡ ምርጫ በጥቅሉ ሴት አርሶ-አደሮች እንደ ማዳበሪያ፣ አረም ማጥፊያ (ፔስቲሳይድ፣ ሄርቢሳይድ እና ፈንጊሳይድ) እና መሰል ዘመናዊ የግብርና ግብዓቶችን የመጠቀም ደረጃቸው ከወንድ አቻዎቻቸው 2 በመቶ (2 percentage points) ገደማ ያነሰ በመሆኑ ይህ ሁኔታ የፆታ የምርታማነት ልዩነቱን እያሰፉ ከሚገኙ ምክንያቶች አንዱ ያደርገዋል፡፡ የማዳበሪያ አጠቃቀምን በተመለከተ የሴት አርሶ አደሮች ተሳትፎ ውስን የመሆኑ ጉዳይ የሚያያዘው ማዳበሪያ ወጪ የሚጠይቅ ግብዓት ከመሆኑ ጋር ሲሆን፣ በተጨማሪም ማዳበሪያ አንድ ጊዜ በብዛት የሚቀርብ ግብዓት መሆኑ፣ ይህም ከፍተኛ ኢንቨስትመንት የሚጠይቅ መሆኑ ለሴት አርሶ አደሮች በቀላሉ ለማግኘት የግብርና ግብዓቶች አዳጋች ያደርገዋል፡፡ ይህ በተለይ የገንዘብ እጥረት ላለባቸው ሴት አርሶ አደሮች ከባድ ፈተና ነው፡፡ በሌላ በኩል ሴቶች ለትራንስፖርት ተደራሽነት ግልጋሎት ተደራሽ ባለመሆናቸው፣ በተለይ ራቅ ያሉ አካባቢዎች የሚኖሩ ሴት አርሶ አደሮች ማዳበሪያ በቀላሉ ገዝተው ወደ ማሳቸው ለመውሰድ ይቸገራሉ፡፡ 3.  ሴቶች ከሥራ ፈጠራ እና ከግል የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሚያገኙት ገቢ ከወንድ አቻዎቻቸው በእጅጉ ያነሰ ለመሆኑ የግብዓት አጠቃቀም ልዩነቱ ዋነኛ ተጠቃሽ ምክንያት ነው፡፡ በዚህ ረገድ በአማካይ ሴት የሥራ ፈጣሪዎች ወርሃዊ ሽያጭ ከወንድ የሥራ ፈጣሪዎች ጋር ሲነፃፀር 79 በመቶ ቀንሶ ይታያል፡፡ ይህም በምርት ግብዓቶች አጠቃቀም ረገድ ያለው ልዩነት ግምት ውስጥ ሳይገባ ነው፡፡4 ነገር ግን የምርት ግብዓቶች ከግምት ውስጥ ሲገቡ ይህ የፆታ ልዩነት ወደ 24 በመቶ ይወርዳል፡፡ እዚህ ላይ የሚያስገርመው ጉዳይ በወርሃዊ ሽያጭ ዙርያ የሚታየው ልዩነት የምርት ግብዓቶችን የመጠቀም ደረጃን እንጂ ግብዓቶችን ውጤታማ ከማድረግ አንፃር ያለውን ልዩነት የሚያመላክት ያለመሆኑ ነው፡፡ በሌላ ቋንቋ ሴቶች የወንድ 4 እነዚህ ግኝቶች የተመሠረቱት ወካይ የሆነ 1,822 ድርጅቶች እና 1,600 ዋና ሥራ አስኪያጆች ናሙና ላይ ሲሆን፣ በናሙናው ከተወሰዱት ዋና ሥራ አስኪያጆች 40 በመቶው ሴቶች ናቸው፡፡ 4 አቻዎቻቸው የሚጠቀሙትን የምርት ግብዓት በእኩል መጠቀም ቢችሉ በወርሃዊ ሽያጭ ረገድ የታየው ልዩነት በእጅጉ የሚቀንስበት ዕድል እንዳለ ግኝቶቹ ያስረዳሉ፡፡ በዚህ ረገድ በግል ስራ ከሚገኝ ገቢ ዙርያ በወንድ እና ሴት ተቀጣሪዎች መካከል የሚታየውን የገቢ ልዩነት እና በዚህ መስክ ከፍተኛ ግፊት የሚያሳድሩ ምክንያቶችን ቀጥሎ እንዘረዝራለን፡፡ ሴቶች (ሥራ ፈጣሪ ሴቶች) በግል ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ዙርያ የሚያጠፉት ሰዓት ውስን መሆን በገቢ ረገድ ከወንድ አቻዎቻቸው ጋር ልዩነት እንዲኖራቸው አድርጓል፡፡ ለምሳሌ በጥናቱ መሠረት በሥራ ላይ የምትጠፋ አንድ ተጨማሪ ሰዓት በስተመጨረሻ በወርሃዊ ሽያጭ ላይ ቢያንስ የአንድ በመቶ ጭማሪን የማስመዝገብ ኃይል አላት፡፡ በግል ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ የተሰማሩ ሴቶች በአማካይ በሳምንት 17 ሰዓት ሥራ ላይ የሚያጠፉ ሲሆን፣ ይህም ከወንድ አቻዎቻቸው 23 ሰዓት ጋር የ6 ሰዓት ልዩነት ያሳያል፡፡ ሴቶች በሥራ ላይ የሚያጠፉት ጊዜ ማነስ በብዙ ምክንያቶች የመጣ ነው፡፡ በዋነኝነት ግን በቤት ውስጥ ካላቸው በቢዝነስ ኃላፊነት ጋር በተያያዘ አለበለዚያም እንደ ማታ ላይ ያሉ ጊዜዎችን መጠቀም ያለመቻል ዓይነት ምክንያቶች (ከደህንነት ጋር እንቅስቃሴ ዙርያ በተገናኘ) ይገኙበታል፡፡ የሚጠፋ ጊዜ ሴት የሥራ ኃላፊዎች ከወንድ አቻዎቻቸው ጋር ሲነፃፀሩ በአማካይ በ0.3 ያነሰ ቁጥር ያላቸው ሠራተኞችን ቀጥረው የሚያሠሩ ሲሆን ይህም በገቢ ደረጃ ለሚታየው የፆታ ልዩነት የራሱን አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ በመሆኑም ወንድ የሥራ ኃላፊዎች የተሻለ የሠራተኛ ቁጥር ስላላቸው ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ በሌላ በኩል እያንዳንዱ ተቀጣሪ ሠራተኛ በወንድ የሥራ ኃላፊዎች በሚመሩ ድርጅቶች ውስጥ በወርሃዊ ሽያጭ ላይ 4.5 በመቶ ጭማሪ እንዲመዘገብ እገዛ የሚያደርግ ሲሆን፣ በሴት ኃላፊዎች በሚመሩ ድርጅቶች ግን ይህ አስተዋጽኦ ወደ 3.6 በመቶ ቀንሶ ይገኛል፡፡ በሴቶች የሚመሩ ድርጅቶች አካባቢ ያነሰ የሠራተኛ ቁጥር የመኖሩ የሰው ኃይል ምክንያት በዋነኝነት የሴቶች ፋይናንስ አቅርቦት ተደራሽነት ውስን መሆኑ ነው፤ ከዚህ ባለፈ ሴቶች የሚመሩዋቸው ድርጅቶች አቅርቦት የሥራ ላይ ሥልጠና የማዘጋጀት ዕድል አናሳ መሆን እና በአጠቃላይ ጠንካራ የቢዝነስ ትስስር ያለመኖር ለተቋማቱ አለማደግ እና የቅጥር አቅማቸው እንዳይጨምር ምክንያቶች ሆነው ይቀርባሉ፡፡ ተገቢው የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶችን ከማንቀሳቀስ አንፃርም በጥቅሉ ሴት የሥራ ኃላፊዎች ከወንድ አቻዎቻቸው ጋር ሲነፃፀሩ ከፍተኛ ልዩነት አላቸው፡፡ ይህም በገቢ ረገድ በፆታዎች መካከል ያለውን ልዩነት ያሰፋዋል፡፡ በዚህ ረገድ 15 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች ቢያንስ አንድ የንግድ ፈቃድ ያለው ድርጅት የሚያስተዳደሩ ሲሆን ይህ ምጣኔ በወንዶች ረገድ ወደ 37 በመቶ ከፍ ያለ ነው፡፡ ሴቶች የንግድ ፈቃድ ያለው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የማድረግ ዕድል አንሶ የመገኘቱ ምክንያት ዘርፈ ብዙ ቢሆንም በዋነኝነት ግን ሴቶች ፈቃድ ለማውጣት የሚጠይቀው ገንዘብ እና ጊዜ ውስንነት እንዳለባቸው፤ ከዚያ ባለፈም የአገሪቱን የንግድ ፍቃድ ቢሮክራሲ ተቋቁመው የንግድ ፈቃድ ለማውጣት የእውቀት እና የክህሎት ውስንነት ሊኖርባቸው እንደሚችል መገንዘብ ይቻላል፡፡ ሴቶች የቢዝነስ ብድር የማግኘት ዕድላቸውም ቢሆን ከወንዶች በ4 በመቶ ያነሰ ነው፣ ብድር ሲያገኙም የብድር መጠኑ ከወንዶች በ50 በመቶ ያነሰ እንደሚሆን ግኝቶቹ ያስረዳሉ፡፡ እዚህ ጋር የሚያስገርመው ሌላው ጉዳይ የቢዝነስ ብድር ማግኘት በሽያጭ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያለው መሆኑ ነው፡፡ በሌላ በኩል የሚገኘው የብድር መጠን ደግሞ ከሽያጭ ጋር አዎንታዊ የሆነ ቁርኝት እንዳለው ይታያል፡፡ ዞሮ ዞሮ ሴቶች የሚያገኙት የቢዝነስ ብድር በጣም ዝቅተኛ ከመሆኑ አንጻር በጾታ ልዩነቱ ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ አያመጣም፤እንደውም ያሰፉዋል፡፡ የመደበኛ ብድር አቅርቦት 5 4.  እንደ ዕድሜ፣ የጋብቻ ሁኔታ እና የትምህርት ደረጃን ከመሳሰሉ ጥቂት ወሳኝ ባህሪያት ውጪ በቅጥር ገቢ ዙርያ በወንዶች እና ሴቶች መካከል ያለውን ልዩነት በግልዕ የሚያብራሩ ምክንያቶች አይገኙም፡፡ ሰፋ ተደርጐ ሲታይ እንደ ፆታ ላይ የተመሠረተ መድሎ፣ ሴቶች ለቴክኒካል ሥልጠናዎች ያላቸው ተደራሽነት ውስን መሆን እንዲሁም ሴቶች መደበኛ ባልሆነ የሥራ ዘርፎች በብዛት መገኘት ዓይነት ምክንያቶች ለተፈጠረው ልዩነት የተሻለ መንስኤ ሆነው ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡ በኢትዮጵያ የሴቶች የሰዓት ገቢ ከወንድ አቻዎቻቸው በ44 በመቶ ያነሰ ነው፡፡ በግብርና ምርታማነት እና በግል የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ዙርያ የሚገኝ ገቢ ላይ እንደተነሳው በምርት ግብዓቶች አጠቃቀም ደረጃ የሚስተዋሉት ልዩነቶች ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚኖራቸው ቢሆንም፣ የቅጥር ገቢ ልዩነትን ስንመለከት ግን የምርት ግብዓት አጠቃቀም ደረጃን እንኳን ከግምት ውስጥ አስገብተን ወንድ እና ሴቶች በሰዓት የሚያገኙት ገቢ ልዩነት ከ36 በመቶ በታች አይወርድም፡፡ ይልቁኑ በቅጥር ገቢ ዙርያ ያለው ልዩነት መንስኤዎች የተወሰኑ በግልጽ መታየት የማይችሉ ምክንያቶች ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ እነዚህ ነጥረው ያልወጡ መንስኤዎች እንደ ዕድሜ እና የጋብቻ ሁኔታ እንዲሁም የትምህርት ደረጃ ያሉ አንጓ ልዩነት ፈጣሪ ምክንያቶችን አያጠቃልሉም፡፡ ከዚህ ባለፈ በጥናቱ ያልተካተቱ በግልጽ የማይታዩ ምክንያቶችም በቅጥር ገቢ ዙርያ የሚንፀባረቀውን ልዩነት በማምጣቱ ረገድ የራሳቸውን ሚና ይጫወታሉ፡፡ እነዚህ መንስኤዎች በአብዛኛው ለመለካት አዳጋች ወይም ግልጽነት የሚጐላቸው ናቸው፡፡ ቀጣዩ ክፍል የቅጥር ገቢ ልዩነት ላይ የራሳቸው የሆነ አስተዋጽኦ ያላቸው አንዳንድ ባህርያት ዙርያ ዝርዝር መረጃ ለመስጠት ይሞክራል፡፡ ዕድሜ በጥቅሉ በቅጥር ገቢ ላይ አዎንታዊ የሆነ ተፅዕኖ አለው፡፡ በዚህ ረገድ በሴት እና ወንድ ተቀጣሪ ሠራተኞች መካከል በአማካይ የ5 ዓመት የዕድሜ ልዩነት የሚንፀባረቅ ሲሆን፣ ይህም የገቢ ልዩነቱን እንዳሰፋው መገንዘብ ይቻላል፡፡ በሌላ በኩል ጋብቻ በገቢ ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል፡፡ በዚህ ረገድ 65 በመቶ የሚሆኑት ወንድ ተቀጣሪ ሠራተኞች በትዳር የሚኖሩ ሲሆን፣ በሴቶች በኩል ግን 45 በመቶ ብቻ ባለትዳር ናቸው፡፡ ይህ ሁኔታ የፆታ የገቢ ልዩነቱን የሚያባብስ ነው፡፡ የትዳር አጋራቸው በሞት መለየት ወይም በፍቺ መለያየትም ቢሆን ከገቢ ጋር ያለው ቀጥተኛ ግንኙነት አዎንታዊ ነው፡፡ ወደ 6 በመቶ የሚሆኑት ወንደ ዕድሜ እና የትዳር ተቀጣሪዎች በሞት ወይም በፍቺ ትዳራቸው የፈረሰ ከመሆኑ ጋር እና ይህ ምጣኔ በሴቶች ወደ 22 በመቶ ከፍ ስለሚል በአጠቃላይ ሁኔታ የፆታ የገቢ ልዩነቱን በማጥበብ ረገድ የራሱ አስተዋጽኦ አለው፡፡ የዲፕሎማ ወይም የዲግሪ ምሩቅ መሆንም በተቀጣሪዋች የሰዓት ገቢ ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ ነው ያለው፡፡ በኢትዮጵያ የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ (ባችለርም ሆነ ማስተርስ) የሠራተኞችን የሰዓት ገቢ በ50 በመቶ ሊጨምረው ይችላል፡፡ ይህ በተለይ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ካጠናቀቁ ተቀጣሪዎች አንፃር በግልጽ የሚታይ ልዩነት ነው፡፡ በተመሳሳይ ዲፕሎማም ሆነ ሰርተፍኬት በተለይ የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ካጠናቀቁ ጋር ሲተያይ የተቀጣሪ ገቢን በ20 በመቶ የመጨመር አቅም አለው፡፡ በዚህ ረገድ በጥቅሉ ሴቶች በተሻለ ደረጃ ዲፕሎማ ሥልጠና ይዘው ወደ የሥራ ገበያው የሚቀላቀሉ ሲሆን፣ (22 በመቶ ሴቶች እና 12 በመቶ የትምህርት ደረጃ ወንዶች) በዲግሪ ደረጃ ግን ወንዶች የተሻለ ናቸው፡፡ (20 በመቶ ወንዶች ቢያንስ ባችለር ዲግሪ ያላቸው ሲሆን፣ 11 በመቶ ሴቶች ብቻ ዲግሪ አላቸው)፡፡ ሲጠቃለል በዲፕሎማ እና ምስክር ወረቀት ደረጃ የሴቶች ብልጫ የፆታ የገቢ ልዩነቱን የሚያጠበው ቢሆንም በዲግሪ (ዩኒቨርሲቲ) ደረጃ ግን ወንዶች የተሻለ መሆን የፆታ ልዩነቱን በሌላ አቅጣጫ ያሰፋዋል፡፡ 6  መ ንስኤው በግልጽ ሊቀመጥ የማይችለው የፆታ የገቢ ልዩነት ሁኔታ ከሦስት ዋና ዋና ጉዳዮች ጋር ሊያያዝ ይችላል፡፡ ምንም እንኳን ምክንያቱን በግልጽ ማስቀመጥ ቢያስቸግርም በጥቅሉ ግን 1) ከፆታን መሠረት ያደረገ መድልዎ 2) ከቴክኒካል ሥልጠናና ክህሎትን ማሳደግ እንዲሁም 3) ከኢ መደበኛነት ጋር የሚያያዝ መሆኑን በግልጽ መናገር ይቻላል፡፡ በገቢ ልዩነት ላይ • ፆታን መሠረት ያደረገ መድልዎ፡ በባህላዊው የኢትዮጵያ ከእጅ-ወደ-አፍ የግብርና ዘርፍ በፆታ ላይ ተፅዕኖ ያላቸው የተመሠረተ የሥራ ክፍፍል የተለመደ ተግባር ነው፡፡ በመሆኑም ይህ ሥር የሰደደ ባህልና አስተሳሰብ በግልጽ የማይታዩ ከግብርናው ወደ ግብርና ያልሆኑ ዘርፎች ሽግግር በሚደረግበት ጊዜ በተወሰነ መልኩ ሾልኮ ወደ የቅጥር ባህርያት ሥራ ዘርፉ ሊጋባ እንደሚችል መገመት ስተት አይሆንም፡፡ • ቴክኒካዋ ሥልጠናና ክህሎትን ማጐልበቻ ዕድሎች አቅርቦት፡ ሴቶች በአብዛኛው ከወንዶች ባነሰ በቴክኒካል ሥልጠናም ሆነ ክህሎት ማጐልበቻ ፕሮግራሞች ተሳታፊ የመሆናቸው ጉዳይ አያጠያይቅም፡፡ በሌላ በኩል ሴቶች በተለምዶ ይበልጥ አዋጩ ባልሆኑ ዘርፎች ላይ የታጠረ የሥልጠና ዕድል ያገኛሉ፡፡ በመሆኑም ሥልጠናና በሥራ ገበያው ተፈላጊ የሆነ ክህሎት የቅጥር ገቢን በመወሰን ደረጃ ያላቸው ሚና ከፍተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የሴቶች ገቢ ከወንድ አቻዎቻቸው ያነሰ መሆን በተወሰነ መልኩ ከሥልጠናና ክህሎት ጋር ሊያያዝ ይችላል፡፡ • ኢ-መደበኝነት፡ ሴቶች በመደበኛ የመንግሥትም ሆነ የግል ዘርፍ ተቀጥረው ገቢ ከማግኘት ይልቅ ኢ-መደበኛ በሆኑ ዘርፎች የመሳተፍ ዕድላቸው የሰፋ ስለመሆኑ ከላይ አሳይተናል፡፡ በዚህ ረገድ በኢትዮጵያ 43 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች በኢ-መደበኛው ዘርፍ ተሳታፊ ሲሆኑ፣ ለወንዶች ይህ ምጣኔ13 በመቶ ገደማ ነው፡፡ በአብዛኛው በኢ-መደበኛ ዘርፍ መሳተፍ የሚያስገኘው ገቢ በመደበኛው ከሚገኘው ገቢ ያነሰ በመሆኑ ይህ ልዩነት በአጠቃላይ የፆታ የገቢ ልዩነትን ሊፈጥሩ ከሚችሉ ጉዳዮች አንዱ ሊሆን ይችላል፡፡ 5.  ፆታዊ እምነቶች (norms) ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ላይ ተፅዕኖ ፈጣሪ ወደሆኑ ባህርያት ሊለወጡ ይችላሉ፡፡ በፆታ ዙርያ ለረጅም ጊዜ በማኅበረሰቡ ተይዘው የቆዩ እምነቶች በተለይም ሴቶችና ወንዶች እንዴት ዓይነት ባህሪ ሊጐናፀፉ እንደሚገባቸው የሚደነግጉ እምነቶች ሴቶች በሚመርጧቸው ምርጫዎች እና ዕርምጃዎች ላይ የራሳቸው የሆነ ጫናን ማሳረፋቸው አይቀሬ ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ እነዚህ ባህርያት በሴቶች የኢኮኖሚ ሁኔታ ላይ ተፅዕኖ ይኖራቸዋል፡፡ የሚከተሉት አራት ጫና የሚያሳርፉ ባህርያት ናቸው፡፡ 1) ጋብቻ እና ልጆች ማፍራት 2) መሬትን ጨምሮ ሌሎች ይዞታዎች 3) የቤተሰብ ውስጥ መስተጋብሮች 4) ሥራ እና የግል ሥራ ፈጠራ እንቅስቃሴዎች በመጀመሪያ ጋብቻ በተለምዶ ሴቶች በለጋ ዕድሜ ላይ እያሉ የሚመጣ ነገር መሆኑ አይካድም፡፡ በመሆኑም በተለይ ልጆች የማሳደጉ ኃላፊነት የወጣት ሴቶችን ሥራ የመሥራት ዕድልን ያጠባል፡፡ ሁለተኛ ሴቶች በአማካይ ከወንዶች ያነሰ ንብረት እና ይዞታ ያላቸው ሲሆን፣ ይህም በዋነኝነት በትዳር የተፈራ ሀብትን ማን ነው ባለቤት ሊሆን የሚገባው፣ በፍቺ ወቅትም ቢሆን የንብረት ክፍፍል ጉዳይ ለማን ሊያዳላ ይገባዋል በሚሉት ጉዳዮች ዙርያ ያሉ ሥር የሰደዱ እሴቶች በአብዛኛው ወንዶችን ሲያስበልጡ ስለኖሩ ነው፡፡ በሦስተኛ ደረጃ ሴቶች እና ልጃገረዶች በቤት ውስጥ ያለውን ሥራ የመሸከም ኃላፊነት ስለሚወድቅባቸው በገቢ ማስገኛ የኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ለመሳተፍ የሚኖራቸው ዕድል ጠባብ ነው፡፡ በጨረሻም ሴቶች በራሳቸው ዘንድ የተያዘው ‹‹ለሴት የተገባ ሥራ ይህ ነው›› የሚል ገደብ እንዲሁም መድልዎ በፆታዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ልዩነት ዙሪያ የራሱን ግፊት ሳያሳድር አይቀርም፡፡ ነገር ግን በቅርቡ የተተገበሩ የሕግ ማሻሻያዎች ማለትም የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ እና የገጠር መሬት ምዝገባ መመርያ የሴቶችን ማኅበራዊም እና ኢኮኖሚያዊ ደረጃን ማሻሻል የጀመረ ሲሆን፣ ይህም የፆታ ክፍተቱን ለማጥበብ የራሱን ተፅዕኖ ሊያሳርፍ ይችላል፡፡ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባ የፖሊሲ ዕርምጃዎች ሴቶች፣ በግብርናው፣ በሥራ ፈጠራው፣ እንዲሁም በመደበኛ የቅጥር ሥራ መስኮች ያላቸውን እምቅ አቅም አሟጠው እንዲጠቀሙ ማስቻል በተለይ ኢትዮጵያ አንገብጋቢ የልማት ጥያቄዎቿን ለመመለስ እና የፆታ እኩልነትን ለማረጋገጥ በጣም ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡ በመሆኑም አገሪቱ የጀመረችውን ፈጣን ዕድገት በተሻለ እና ሁሉን አካታች በሆነ ሁኔታ እንዲቀጥል ፖሊሲ አውጪዎች ሊያጤኗቸው የሚገቡ የፖሊሲ አቅጣጫዎች አሉ፡፡ እነዚህ የፖሊሲ አቅጣጫዎች ጥናቱ ያተኮረባቸውን ወሳኝ የሚባሉ በፆታ እኩልነት ላይ ግፊት የሚያሳድሩ ጉዳዮችን በማጤን የተዘጋጁ ምክረ-ሐሳቦች ናቸው፡፡ 7 • ሴቶች ያለባቸውን የጊዜ ጫና የተለያዩ አገልግሎቶችንና ድጋፎችን በማድረግ ለመቀነስ መሞከር፡፡ ይህ በተለይ ሴቶች በቤት ውስጥ ኃላፊነታቸው ዙሪያ ያሉ የጊዜ ጫናዎችን የሚመለከት ነው፡፡ ሴቶች ያሉባቸውን የጊዜ ጫና የሚቀንስ ድጋፍ አገኙ ማለት በቀላሉ በሌላ የገቢ ማስገኛ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ላይ የሚያጠፉትን ጊዜ ጨመረ ማለት ሲሆን፤ ከእነዚህ እንቅስቃሴዎች የሚያገኙት ገቢ እንዲሻሻል እና በገቢ ደረጃ በወንዶች እና ሴቶች መካከል ያለው ሰፊ ልዩነት እንዲጠብ ያስችላል፡፡ • የትምህርት ዕድል ለሴቶች በብዛት መፍጠር፣ ብሎም ሴቶች የሥራ ክህሎታቸውን ማሳደግ የሚችሉበት ቴክኒካል እና ቮኬሽናል ሥልጠናዎችን እንዲወስዱ ማበረታታት፡፡ ሴቶች የትምህርት ዝግጅታቸው የላቀ እንዲሆን ዕድል እንዲፈጠርላቸው፣ እንዲሁም የሥራ ክህሎታቸውን የሚያሳድጉበት ዕድል ቢመቻችላቸው በብዛት በወንዶች ተይዘው ያሉ የሥራ ዘርፎች ላይ ሳይቀር ሴቶች ያላቸው ተሳትፎ የሚቀየርበት አጋጣሚ እየሰፋ ይሄዳል፡፡ ይህም ሴቶች ሥራ ገበያው ውስጥ ያላቸው ተፈላጊነት ብሎም የሚያገኙት ገቢ ከወንድ አቻዎቻቸው ጋር እየተቀራረበ እንዲመጣ በር ይከፍታል፡፡ • በሴት አርሶ-አደሮች ላይ ያተኮረ የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎቶችን ተደራሽ ማድረግ፡፡ የግብርና ኤክስቴንሽን ግልጋሎቶች በተለይ በሴት አርሶ-አደሮች ላይ አተኩረው ከተቀረፁ እና ተደራሽ መሆን ከቻሉ በግብርና ምርታማነት ዙሪያ የሚታየውን የፆታ ልዩነት ለማጥበብ ወሳኝ ሚና መጫወት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ግልጋሎቶቹ በተለይ የግብርና ምርታማነት ልዩነቱን እያባባሱ የሚገኙ የምርት ግብዓቶች ላይ ቢያተኩሩ የፆታ ልዩነቱን በከፍተኛ ደረጃ ለመቀነስ የሚያስችል መሣሪያ መሆን ይችላሉ፡፡ • ሴቶች በተለይ በግብርናና በሥራ ፈጠራው ዘርፍ ወሳኝ የሚባሉ ግብዓቶችን በቀላሉ ማግኘት የሚችሉበትን ሁኔታ ማመቻቸት፡፡ ሴት አርሶ-አደሮችን በተመለከተ የማዳበያ እና አረም ማጥፊያ ኬሚካሎች ተደራሽነትን መጨመር፣ እንዲሁም ሥራ ፈጣሪ ሴቶችን ባማከለ ሁኔታ ደግሞ የሰው ኃይል እና የንግድ ፈቃድ ተደራሽነትን ማሻሻል በምርታማነት እና በገቢ ደረጃ የሚታዩ የፆታ ልዩነቶች በእጅጉ ለመቀነስ ያስችላል፡፡ • የብድር አቅርቦቱ ለሴቶች ተደራሽ እንዲሆን ማስቻልን በተመለከተ በተለይ መካከለኛ የብድር መሣሪያዎች ለሴቶች ተደራሽ እንዳይሆኑ እንቅፋት እየሆነ ያለውን የብድር መያዣ (collateral) ማነቆ ማስወገድ ግድ ይላል፡፡ በዚያውም ሴቶች ለብድር ብቁ (Creditworthy) እንዲሆኑ ማስቻል ያስፈልጋል፡፡ በጂ.አይ.ኤል ጥናት መሠረት ሴቶችን ለብድር ብቁ ማድረግ ማለትም የተበደሩትን የመመለስ አቅም እንዳላቸው እምነትን ለመፍጠር ሁለት የተለያዩ መንገዶችን መጠቀም ይቻላል፡፡ የመጀመሪያው ሴቶች ንብረት እንዲያፈሩ ማድረግ ሲሆን፣ ይህም ለምሳሌ ሴቶች ከትዳር አጋሮቻቸው ጋር የጋራ የመሬት ባለቤት የምስክር ወረቀት እንዲያገኙ በማድረግ ሊፈፀም ይችላል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ አዳዲስ በንብረት ላይ የተመሠረተ የብደር መያዥያን ግዴታ የማያደርጉ የብድር መሣሪያዎችን መፍጠር ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት የብድር መሣሪያዎች ሴቶች በቀላሉ የብድር አቅርቦቱ ተደራሽ እንዲሆንላቸው የሚያስችል ሲሆን፣ ይህም በምርታማነት እና ገቢ ረገድ በተለይ ግብርናው እና የሥራ ፈጠራው ዘርፍ ዙሪያ የሚታዩ የፆታ ልዩነቶችን ለማጥበብ የሚያስችል ነው፡፡ • በማኅበረሰቡ ዘንድ ስር የሰደዱ በፆታ ዙርያ የሚንፀባረቁ እምነቶችን እና ተቋማዊ ማነቆዎችን ማስወገድ፡፡ እነዚህ ማነቆዎች ለዘመናት የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ሲደፍቁ የኖሩ ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከላይ የተጠቀሱት ሥር የሰደዱ እምነቶች እና ተቋማዊ ለተጨማሪ መረጃ ከታች ማነቆዎች በጥናቱ ላይ ለተለዩት የፆታ ልዩነቱ ላይ ግፊት ለሚያሳድሩ ጉዳዮችም ዋነኞቹ መነሻዎች በሚገኘው አድራሻ ያግኙን መሆናቸውም በደንብ ሊጤን ይገባዋል፡፡ ነገር ግን ሊካድ የማይገባው ጉዳይ በቅርብ ጊዜያት እየታዩ ማርከስ ጎልድስቲን ያሉት የሕግ ማሻሻያዎች በተለይ በጋብቻና በንብረት ባለቤትነት ዙርያ እየተተገበሩ ያሉ የሕግ mgoldstein@worldbank.org ማሻሻያዎች እነዚህን ሥር የሰደዱ፣ የተሳሳቱ በፆታ ዙርያ የተያዙ እምነቶች በመቀየር ረገድ ከፍተኛ ተስፋ የፈነጠቁ መሆኑ ነው፡፡ afrgenderlab@worldbank.org 1818 H St NW Washington, DC 20433 USA ይህ ስራ አምብሬላ ፋሲሊቲ ፎር ጀንደር ኢክዋሊቲ (ዩ.ኤፍ.ጂ.ኢ) በተሰኘው የአለም ባንክ ጥምር የድጋፍ ቛት ተደግፏል። ይህ የድጋፍ ቛት በሴቶች እና በወንዶች መካከል ያሉ የኢኮኖሚ ልዩነቶችን ለመለየት እና ብልፅግናን የሚያመጡ መፍትሄዎችን ለምቕረፅ ያለመ ነው። ዩ.ኤፍ.ጂ.ኢ ከኣውስትራልያ ፣ ካናዳ ፣ ዴንማርክ ፣ ፊንላንድ ፣ ጀርመን ፣ ኣይስላንድ ፣ ኔዘርላንድ ፣ ኖርዌይ ፣ ስፔን ፣ ስዊድን ፣ ስዊዘርላንድ ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ ኣግኝቷል። 8